የትግላችን ጉዞ ከዬት ወዴት
ፀሃፊ ፌ ተ ዑመር
ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው በኢትዮጵያ የተከሰተው የለውጥ እንቅስቃሴ እንደማኛውም አገራዊ ለውጥ፤ መጥፎውነና ደጉን፥ አስደንጋጩንና ተስፋ ሰጪውን፤ አሳዛኙንና ኣስደሳቹንም ኣጣምሮበአገራችን እያዘገመ ይገኛል። እስካሁንም ድረስ ቢሆን የለውጡ ሂደት አቅጣቻ ወዴት እንደሚሄድ በእረግጥ ይፋ ባይሆንም፤ አንዳንዴም የጉዞው መስመር ጥርጣሬ ቢያሳድርም፤ አገራችን ወደ ቀናመንገድ በማምራት ላይ እንዳለች ያሚያመላክቱ በርካታ እውነቶች ይታያሉ። በተለያዩ በኢትዮጵያ ምድሮች የሚኖሩ ህዝቦች እርስ በርስ በነበራቸው ግጭት፤ ተወልደው በሰነበቱበት ቀዬያቸውተፈናቅለው በቡዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ሥቃይና እንግልት ደርሶባቸዋል። የተለያዩ የፖልቲካ አመለካከት ያላቸውና፤ በትግል ስልት የሚለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከዚህም ከዚያም ብቅ ብቅ እያሉሕዝቦችን ሲያራብሹና ሲያደናግሩ ቢስተዋሉም፤ እለት ተእለት በአገራችን የሚታዩ እውነታዎች ግን የመረጋጋት፤ የሰላምና የመግባባት ሁኔታዎችን እያጎናፀፉ ይገኛሉ። ለውጡ ከተከሰተ ጀምዝሮኢትዮጵያ ከዴት ወዴት የሚለውን ጥያቄ ልጆቿ በየቀኑ የሚያሰላስሉትና የሚያሳስባቸው ጉዳይ መሆኑ ለማንም ስውር አይደልም። ከረዥም ዐመታት ስቃይና መከራ በሗላ አሁን ለሕዝባችንየመጣው የለውጥ ብርሃን ከእጃችን በዋዛ እንዳያመልጥ፤ ወገን ሁሉ፤ በከፍተኛ ደረጃ እንክብካቤ ማድረግ ይጠበቅበታል።
መከራንና ችግርን ለረዥም ዐመታት ተላብሶ ለሰነበተ ሕዝብ፤ ከችግሩ ለአንዴና ለሁሌም እንዲላቀቅ፤ አገራችንን ወደፊት ለማራመድ፤ ያገኘናቻውን ድሎች እንደ ዐይን ብሌን መጠበቅ የግድ ይላል።በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በየአካባቢያቸው፤ ይህን ያገር ጉዳይ ትክክለኝ አቅጣጫ ለማስያዝ፤ ከፍትኝ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ይህን በጎ ምግባርን ማበረታታት ከሁሉምዜጋ የሚጠበቅ ኃላፊነት ሲሆን ለዚሁ ተግባር ተምሳሌት በመሆን በሀረሪ ክልልም አንዳንድ ጥረቶች እየተስተዋሉ ነው።
እንደሚታወቀው የሀረሪ ክልል በሁለት የብሔረሰብ አካሎች ማለትም በሀረሪና በኦሮሞ ሕዝብ ተወካዮች በጣምራ የሚስተዳደር ክልል ነው። እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች በታሪካቸው ለምእት ዐመታትአብረው በሰላምና በመቻቻል ከመኖር አልፈው፤ ክልላቸውንም ተደጋግፈው በማስተዳደር ከሃያ ዐመታት በላይ አሳልፈዋል። ምንም እንኳን በአሠራር ዙሪያ አንዳንድ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ የተስተዋሉ ቢሆንም፤ በአብላጫው ግን ክልሉ በመቻቻልና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ነበር። ይህ ክልል ግን ከመቻቻል አልፎ የነዋሪውን ሕይወትየሚጠቅምና ከተላበሰው ችግርም ለማላቀቅ ኣንዳችም ሥራ እንዳልተሠራ የሚደበቅ ሃቅ አይደለም። ሕገ መንግሥቱ በፈቀደለት እድል ተጠቅሞ ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ በጎ ሥራ አልተገበረም። ስለዚህም ነው በአገራችን የለውጥጮራ ሲፈነጥቅ፤ የሀረሪ ህዝቦችም፤ እንደ ማንኛውም ዜጋ፤ ለውጡን በእልልንታና በሆይታ የተቀበሉት። በዚህች አጭር የለውጥ ፍንጣቂ፤ ሀረሪዎችም ፅዋቸው ሆኖ፤ ለውጡ ይዞት ያመጣውንየነፃነትና የሰላም ጮራ፤ አብሮት ካስከተለው ችግርና ገፈት ጋር የተጋሩት። የሀረሪ ህዝቦች ከሺ ዐመታት በላይ በባለቤትነት በኖሩበት መሬት፤ አንዳንድ የሁለቱን ህዝቦች ወንድማማችነትና አብሮበሰላም መኖር እንቅልፍ ያሳጣቸው ቡድኖች፤ ክልሉን በጠብ ለማናዋጥ ሙከራ ቢያደርጉም፤ ይህ በሕዝቦች ላይ የተሰነዘረው ጥቃት ግቡን ሳይመታ ወድሟል። ሁለቱ ሕዝቦችም ከዚህ አስከፊድርጊት አንድ ኣላቅ የቀሰሙት ትምህርት ቢኖር፤ በከፍተኝ ትግል የተጎናፀፉትን ነፃነት፤ ሰላምና ከሁሉም ጋር ተስማምቶ አብሮ የመኖርን ባህል ተግተው መጠበቅ እንዳለባቸው ነው።
መቸም ትግልን ወደሚፈለግበት ግብ ለማድረስ፤ ቀጥተኛ ሳይሆን ብዙ ውጣ ውረድ የሞላበት ጉዞ እንደሚጠብቅ እሙን ነው። በመሆኑም የክልሉ ነዋሪዎች ባገኙት እድል ቸል ሳይሉ፤ ለውጡን እንደጨቅላ ህፃን መንከባከብ እንዳለባቸው አጥብቀው የተረዱት እውነት ነው። በሀረሪ፤ በኦሮሞና በክልሉ በሚኖሩ ሌሎች ህዝቦች መሃል መግባባት፤ መተባበር፤ ሰላም እንዲሰፍን ጥረት ማድረግ፤በክልሉ ውስጥ ለሁሉም የሚደርስ ብልፅግና እንዲመጣ፤ ወገብን አጥብቆ መስራት ፤ የያንዳንዱ ግለሰብ ኃላፊነት ነው። ከዚህ ቡፊት በሀረሪ ክልል የተፈፀመውን በደል ፤ ዳግም እውን እንዳይሆንከፍተኝ ትግልና ትጋት ይጠይቃል። የክልሉ ሕዝቦች በጉጉት የሚጠብቁት ጉዳይ ቢኖር፤ ክልሉ በኤኮኖሚ በልፅጎ እነሱም የብልፅግናው ተቋዳሽ መሆንን ነው። የክልሉ መሪዎችም ይህንን ሃቅ አንድብለው፤ የሥራቸው ተቀዳሚ ዐላማ አድርገው፤ የራስ ጥቅምን ወደሗላ ትተው፤ የህዝብ አገልጋይ መሆን ተግባራቸው እንደሆነ መገንዘብ ይሮርባቸዋል።
የክልሉን ህዝቦች ጥቅም ለማስጠበቅና፤ ነዋሪዎቹም እድገትና ብልፅግናን እንዲጎናፀፉ ለመርዳት፤ ከሁሉም ህዝቦች፤ ድርጅቶችና ግለሰቦች፤ ወገን ሳይለይ፤ በጋራ ለምሥራት ”የሀረሪ ትብብርለፍትሕና እኩልነት” ፤ በሀረሪ ተወላጆች የተመሠረተ ድርጅት ነው። ህዝቦች እርስ በርሳቸው እንዲግባቡ፤ አብረው በጉርብትናና በሰላም እንዲኖሩ፤ በአእምሮና በኤኮኖሚ በልፅገው አኩሪቤተሰብ እንዲያፈሩ፤ ለከባቢያቸውና ለመላው ኡትዮጵያም የሚፈይዱ እንዲሆኑ፤ የሚጠበቅበትን ለመፈፀም በቁርጠኝነት ተነሳስቷል። የክልሉ ህዝቦችም ለዚህ ለተቀደሰ ዐላማ ከጎናችን ተሰልፈው፤ግባችንን እንድንመታ አጋርና ተካፋይ እንዲሆኑ፤ በዚብ አጋጣሚ ጥሪያችንን በትህትና እናቅርባለን። ጉዟኣችንም የሰላም፤ የመቻቻል፤ የነፃነትና የብልፅግና እንዲሆን የልብ ምኞታችን ነው።
Disclaimer-
The views and opinions expressed here are those of the author and do not necessarily reflect the official policy or position of Harari Alliance for Justice & Equality (H.A.J.E.).