Press Release

በጭፍን ለስልጣን የሚታዘዙ ሰዎች መቼም ነፃ አይሆኑም።

በጭፍን ለስልጣን የሚታዘዙ ሰዎች መቼም ነፃ አይሆኑም።
በ25ኛው የሀረሪ ስፖርትና ባህል በዓል የየተስተዋሉ በጎ ፣ መጥፎውእና አስቀያሚ ክስተቶች
የሀረሪ ትብብር ለፍትህና እኩልነት መግለጫ

____________________________________________
ባለፈው ሳምንት በቶሮንቶ፤ ካናዳ በዲያስፖራና በአገር ቤት ባሉ ሀረሪዎች በተካሄደው 25ኛው የሀረሪ ስፖርትና ባህል በዓል ዝግጅት ላይ፤ ሀረሪዎች እንዴት የባለስልጣናት ተገዢ እንደሆንን ተመልክተናል። እነዚህ ባለስልጣኖች በሐረር ህዝቦችን፤ መሠረታዊ፤ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን፤ ደህንነታቸውንና ሌሎችንም መብቶች እንደ ማህበረሰብ የነፈጉ ናቸው። ይህ የህልውና ስጋት በህዝባችን ጭንቅላት ላይ ቢያንዣብብም፤ የደስታ ስሜት የነበራቸው የሀረሪ ቶሮንቶናውያን ከመላው አለም የመጡትን ሀረሪዎች ከአቅማቸው በላይ መስተንግዶ አድርገው ተቀብለዋል። የሀረሪ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በ1995 በአትላንታ፤ ጆርጂያ የተጀመረ እውነተኛ የሀረሪዎች ተቋም ነው። ይህ ሃያ አምስተኛውን አመት የምስረታ በዓሉን ስናከብር፤ ሀረሪዎች ለዝግጅቱ መስራች አባቶች፤ ምስጋና ማድረስ እንወዳለን። የካናዳ ሃይለኛ የሓምሌ ሙቅት ሳይበግራቸው፤ በቶሮንቶ የሚገኙ ሀረሪዎች፤ ከቅርብና ከሩቅና የመጡትን እንግዶች መግቧል፣ በደስታ አስተናግዶአል። ከሁሉም በላይ ግን፤ በተለይ በህጻናት እና ጎልማሶች ላይ የማይረሱ ትዝታዎችን ጥሎአል። ነገር ግን በቶሮንቶ ባለፉት ሰባት ቀናት በተካሄደው በዓል፤ ሀረርና ሀረሪዎች በከፍተኛ አደጋ ላይ ባሉበት ወቅትና፤ አገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን ስቃያቸውንና የፖለቲካ ጉዳዮቻቸውን ማሰማት በሚያስፈልግበት ወቅት፤ በዓሉን በደስታንና በጭፈራ ብቻ ማሳለፍ አግባብ እንዳልሆነ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነበር። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ከተዘጋጁት መድረኮች አንዱ የሀረሪ ትብብር ለፍትህና እኩልነት (HAJE) ሲያዘጋጅበት የነበረው የመህበረእብ ስብሰባ ነው። ይህ ዝግጅታችን ግን በእለተ ቀኑ ዋዜማ በበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴው ባልታወቀ ምክንያት ተስተጓጉሏል ።

 

ያመለጠው እድል። (Missed Opportunity)
___________________________
የሀረሪ ህዝብ ችግሮችንና፤ በሀረሪዎች የተጋረጠውን አስከፊ ሁኔታ ለመቅረፍ፤ የሀረሪ ትብብር ስብሰባውን ለማካሄድ ላለፉት አራት ወራት ሲዘጋች ነበር። የሀረሪ ትብብር፤ ለሁላችንም ውድ በሆኑ ጉዳዮች ምክራቸውን እንዲለግሱንና ከታዳሚውቻችን ጋር እንዲያወያዩን፤ ሀረሪውችንና የሀረሪ ወዳጆችን ጋብዘን ነበር። እኛ ሀረሪዎች ስላጋጠመን ከፍተኛ ቀውስ አስደላጊውን መረጃ ለመስጠት እስከ መጨረሻው ዝርዝር እቅድ አውጥተን፤ ሀረሪ ወገኖቻችን በአካልም ሆነ በድምፅ ማጉላት የሚሳተፉትንና ሀሳባቸውንም የሚሰጡበት መድረክ አዘጋጅተን ነበር። ይህን ዝግጅታችንን በእቅዳችን መሠረት ብናከናውን ሀረሪዎች በእጅጉ ተጠቃሚ እንሚሆኑ ጥርጥር የለንም። ግን የታሰበው አልሆነም። በቅርቡ የማህበረሰባችንን ችግሮች ለመፍታትነ ለመወያየት ሌላ የውይይት መድረክ እንደሚኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

በጎው ነገር (The Good)
_______________
በዚህ በዓል፤ ሳምንቱን በሙሉ፣ ጓደኞች እና ቤተሰቦች ተገናኝተው ተዋውቀዋል። ለረዥም ዓመታት ያልተገናኙ ሀረሪዎች ወርቃማ ጊዜ አሳልፈዋል። ለብሁ ጊዜ ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን እርስ በእርስ ለማስተዋወቅ እድል አግኝተዋል። የህብረተሰብ ግንኙነት ዳብሮአል። ይህ ስብስብ የሀረሪ ማህበረሰብ ግንባታና የግንኙነት ስሜትን አጠናከሮአል። ወጣቶቻችን ስለ ቅርሶቻቸው እና ባህላቸው ትምሕርት ቀስመዋል። በድምቀቱ የሚታወቀው የሀረሪ ባህል ልብስም በዓሉን አእሳምሮታል። ባህላዊ የሀረሪ ምግቦች፤ እንደ ሑልበት መራኽ፣ ዋቃሊም፣ ፋጢራና ሀሪስ በመቅረባቸው የበዓሉ ተካፋዮችን አስደስቶአል። እንደተለመደው የሀረሪ ሙዚቃም ለበዓሉ ከፍተኛ ድምቀት ስጥቶታል።

መጥፎው ነገር (The Bad)
_______________
በዚህ አመት አብዛኛዎቹ የበዓሉ ተሳታፊዎች ጎልማሶች እንደነበሩ ተስተውሏል። ወጣቶቹ የመጪው ትውልድ ተስፋ ናቸውና ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር በቁም ነገር ካላስገባን የሐረሪዎች የወደፊት ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ጥርጥር የለውም። በዚህ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዓል፤ ሁላችንም ራሳችንን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ በቂ ሥራ ሰርተናል ወይ? ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፣ የዚህ ትልቅ የሀረሪ ስብስብ ጭብጥ ወይም ዋና የመነሻ መልእክት ምን ነበር? በ25ኛው የሀረሪ ስፖርትና ባህል በዓል ላይ ምን አስፈላጊና ተጨማሪ ሥራ መሰራት ነበረበት? የሚለው ጥያቄ በኛ ግምት በቅጡ አልታሰበበትም እንላለን። በቅርጫት ኳስ ሜዳና በእግር ኳስ ሜዳ ከጓደኞቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሀረሪዎች ከፍተኛ ደስታ ቢሰማቸውም፤ በዚህ ሁሉ ትልቅ አከባበር የተረሳ ወይም ችላ የተባለ ጉዳይ ነበረ ወይ? የሀረሪ ወጣቶች ሐረር ያለችበትን ቀውስ በአግባቡ ተረድተዋል ወይ? ቢባል መልሱ በፍጹም ይሆናል።

አስቀያሚው ነገር (The Ugly)
_________________
እንደ ማህበረሰብ በጭፍን ለስልጣን ታዛዥ የመሆን ባህሪ፤ ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ተስተውሏል። ለስልጣን በጭፍን መታዘዝ፤ ሰዎች

በኃላፊነት ላይ ያሉትን ለማስደሰት ወይም በጭፍን ለመታዘዝ የመሞከር ዝንባሌ ነው። ሰዎች ህጋዊ ስልጣን አላቸው ብለው የሚያምኖአቸውን በጭፍን ያከብራሉ፤ ይከተላሉ። ህዝባችን ይህንን ባሕርይ ልማድ አድርጎ የያዘው፤ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ የሀረሪ ምንግሥት ለይስሙላ ከተመሠረተ ወዲህ ነው። በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ምክንያት ሀረሪዎች አሁንም የህልውና ስጋት ውስጥ ወድቀዋል። በሐረር ያለው እውነታ ይህ ሆኖ ሳለ፤ ጉዳዩን በቸልታ አይቶ እንዳላዬ ማለፍ እንደሰው ሊያስገርመን ይገባል። በማጠቃለልም የሀረሪ ትብብር ለፍትህ እና እኩልነት (HAJE) ሀረሪውችን በሚጎዱ ጉዳዮች ላይ ማህበረሰባችንን ለመደገፍ ሁሌም ይተጋል። የሀረሪ ህብረት በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሀረር እና የሀረሪውችን ጥቅም ለማስጠበቅ የቆመ የፖለቲካ ተሟጋች ቡድን ነው።

ከዚህ የሚከተለው፡ የሀረሪ ስፖርትና ባህል 25ኛ ክብረ በዓል ሲከበር ታቅዶ በነበረው የውይይት መድረክ ላይ በሐረሪ ትብብር ለፍትህና እኩልነት (HAJE) ተዘጋጅቶ የቀረበ የአቋም መግለጫ ነው።

የውይይት መድረክ ዝግጅቱን፤ የሐረሪ ትብብር እንዲያዘጋጅ ሃላፉነት የተሰጠው ቢሆንም፤ በበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴው ጣልቃ ገብነት እና ትብብር ማነስ ምክንያት የሐረሪ ትብብርሀ ዝግጅቱን መልሶ ለአዘጋጆቹ በጁላይ 04, 2023 ለማስረከብ ተገዶአል። የአቋም መግለጫው የሚያተኩረው በሐረር ባለው ቀውስ ላይ ሲሆን፤ በሐረር ከተማ የሐረሪ ማህበረሰብን ባጋጠሙት አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ አቋም ወስዶአል። ስለሆነም፤ የሐረሪ ትብብር ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት የአቋም መግለጫውን ማቅረብ ይፈልጋል።

1. ከረዥም ጊዜ ጀምሮ፡ በሀረር የሀረሪዎችን ጥቅም የሚወክልና፤ ትግላቸውን የሚመራ ድርጅት አለ ብለን አናምንም። በሐረሪ ክልልበአመራርነት የተቀመጡትን ባለስልጣናት፤ ለሕዝቡ የገቡትን ቃለ መሃላ በማክበር፡ የሀረሪዎችን ጥቅም እንዲያስከብሩ፣ ለሐረሪዎች ዓላማ ሌት ተቀን እንዲታገሉ፣ ሐረሪዎችን በእለት ተዕለት ትግላቸው እንዲረዱና እንዲደግፉ በጥብቅ ልናሳስባቸው እንወዳለን። እና ለሀረሪ ህዝብ የገቡትን ቃል ኪዳንም ለአላህ የገቡት ቃል ኪዳን መሆኑን እንዲያስታውሱና ፤ ባአላህ ፊትም በፍርድ ቀን እንደሚጠየቁ ማስታወስ እንወዳለን።

2. የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ከተፈጠረ ጀምሮ፤ የሀረሪዎች እርሻ ንብረቶችና መኖሪያ በቶች በሕገ ወጥ መንገድ መዘረፋቸው ጸሐይ የሞቀው ሃቅ ነው። የክለሉ ባለስልጣኖች፤ ህጋዊ ግዴታቸውን ተወጥተው በመቶዎች ለሚቆጠሩ የሀረሪ ተወላጆች ንብረቶቻቸውን እንዲመለስላቸው እንጠይቃለን። የንብረቱ ባለቤቶቹ ለረዥም ጊዜያት የደረሰባቸውን ግፍና ወከባ፤ ተገቢውን ካሳ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን።

3. የሐረሪ ታሪካዊ ትምህርት ቤቶችና መስጂዶች ባለፉት ሦሥት አስርት አመታት ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸዋ። አሁን ደግሞ ፍፁም ውድመት ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህን ቅርሶች ለመጠገንና በአግባቡ መንከባከብ የክልሉ ባለስልጣናት መሰረታዊ ግዴታዎች ናቸው። ታዋቂው ተቋም፣ አው አብዳል ትምህርት ቤት እና መስጂድ፤ ለዚህ ትልቅ ምሳሌ ነው። ይህ ተቋም የተመሰረተው ከሃምሳ አመት በፊት ሲሆን፤ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ሙሉ በሙሉ በሐረሪዎች መዋጮ የታንጸ ነው። ዛሬ አብዛኛው ንብረቱ በህገ ወጥ መንገድ በሌሎች የተወረሰ ሲሆን ትምህርት ቤቱን መጠገን የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሶአል። ህግን ማስከበር የባለስልጣናቱ ግዴታ ስለሆነ፤ ሀላፊነታቸውን በተገቢው ለመወጣት፤ የአው አብዳልን ትቓም ወደ ትክክለኛው የሀረሪ ባለቤትነት እንዲመልሱልን እና ትምህርት ቤቱንም መስጂዱንም እንዲጠግንኑ እንጠይቃለን።

4. የሐረርን ታላቅነት፤ ታሪክ በተለያዩ ወቅቶች በሚገባ ዘግቦታል። በታሪክ፤ ሀረርና አዋሳኝ ግዛቶች፤ የተስተካከለ ኢኮኖሚ፣ አስተዋይ የፖለቲካ አመራር፣ የበለፀገ ባህል፤ በኢትዮጵያና በዓለም ታሪክ ውስጥ አንጋፋ ቦታ ነእንደነበረው የታወቀ ነው። ይህንን የሀረር እና የሀረሪዎችን ታላቅነት ቅርስ ባልስልጣናቱ በልባቸው ስርጸው፤ ህብረተሰቡ ተደራጅቶ ለመብቱ እንዲታገል፣ ሀረሪዎች የሚጠብቃቸውን ተግዳሮቶች እንዲገነዘብ ማድረግ እና ሀረሪዎች በማንነታቸው እንዲኮሩ ማድረግ የሀረሪ ባለስልጣናት ግዴታ ነው። ሀረሪዎች ሀረር የነሱ እንደሆነች በልባቸው እንዲያምኑና፤ ሀረርንም ለመጠበቅና ለማሳደግ እንዲጥሩ ማድረግ የነሱም የመላው ሀረሪዎችም ጌታ እንደሆነ አጥብቀን እናሳስባለን።

5. በሐረር ውስጥ ካሉት አሳዛኝ እውነታዎች አንዱ የወጣቶች ሥራ አጥነት ከመቼውም ጊዜ መናሩ ነው። ለሁሉም የሐረሪ ተወላጆች ውጤታማና ትርጉም ያለው ሥራ የመፍጠር ተግባር በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ግዴታ ነው። ተገቢውን ሥልጠና መስጠት፣ በአጠቃላይ የሀረሪዎችን ለራስ ክብርና ግምት ለማበልፀግ ፕሮግራሞችን መፍጠር የባለሥልጣናት ግዴታም፤ ሀላፊነትም ነው። እናም፤ ይህም በተቻለ ፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆን እንጠይቃለን።

6. የሐረሪ ክልላዊ መንግስት አላማን ማክበርና መተግበር በሐረር ስልጣን ላይ ያሉ አካላት ግዴታና ኃላፊነት ነው። በክልሉ ሕገ መንግሥት ውስጥ በግልጽ የተቀመጡት ሕጎች እንደሌሉ ተቆጥረውና፣ ተዳክመው፤ ከዚያም በላይ እብዛኛው ህጎች ባለመተግበራቸው፤ አጠቃላይ የክልሉን አስተዳደር ጽንሰ-ሐሳብ ትርጉም አልባ እድርገውታል። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋዎች በየክልሎቻቸው የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ዋስትና ሰጥቷል። የሀገሪትዋ ህገ መንግሥት፤ የሁሉም ብሔረሰቦች ቋንቋዎች፤ በትምህርት ቤቶች፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ፍርድ ቤቶች፣ ወዘተ መተግበር እንዳለባቸው ይደነግጋል። ነገር ግን ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ባለው ጊዜ “ራስን በራስ የማስተዳደር” መርህ በሐረር እልተከሰተም። በስልጣን ላይ ያሉት አካላት የሀረሪ ባህልን እንዲያከብሩና እንዲንከባከቡ፤ የሀረሪ ቋንቋም እንዲዳብር፣እንዲያብብ እና የክልሉ ይፋዊ ቋንቋ እንዲሆን እንጠይቃለን።

7. የሀረሪ ክልል ተወላጆች፤ በክልሉ የጸጥታ አካላት ስጋት ውስጥ ስለወደቁ የመንግስትን ሐሳብ የሚቃወሙ ግለሰቦችና ቡድኖች እጣቸው እስር ቤት እንድሆነ ይናገራሉ። ሀረሪዎች እርስ በእርሳቸው እየተጠራጠሩ ሃሳባቸውን ለመግልጽ ፍራቻ አለባቸው። ነፃና ዲሞክራሲያዊ ውይይት የነፃና ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ የማዕዘን ድንጋይ ነው። ይህ ከሌለ ሥርዓቱ ወደ አምባገነንነት ይሸጋገራል። ከሶስት አስርት አመታት የስልጣን ዘመን በኋላ፤ ሀረሪዎች የተሻለ ቀን ይመጣል የሚል ተስፋ ሰንጥቀው ቆይተዋል። የሀረሪ ባለስልጣናት፤ ጤናማ ማህበረሰብን ለማስቀጠል፤ ሀሳቦች እንዲያብቡ እና ከተለያዩ ቡድኖች ለሚመጡ አስተያየቶች ክፍት መሆን የግድ ስለሚል፤ ይህ ማህበረሰቡልን ማዋከብና ማስፈራራት በአስቸኮይ እንዲቆም እንጠይቃለን።

8. አሁን በግልጽ እንደሚታየው፤ በሐረር የሚታወቅና ውጤታማ የሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የለም። መንግስት ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እና ኩሩ ዜጋ ለማድረግ አዳዲስ የኢኮኖሚ ልማት ሀሳቦችን በማፍለቅ፤ አዋጭና ተግባራዊ መፍትሄዎችን ማምጣት መቻል አለበት። የሀረሪ ክልል ባለስልጣናት፤ ሀረር ያላትን ልዩ እምቅ አቅም ለማሳየትና፤ ለዜጎቿ የበለፀገች ክልል እንድትሆን ከየአቅጣጫው ኢንቨስተሮችን መጋበዝና ማበረታታት ግዴታቸው ነው።

9. በአለም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ብሄረሰቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከህልውና እንደጠፉ ታሪክ ምስክር ነው። በአሁኑ ሰአት፤ እኛ የሀረሪዎች የተያያዝነው የሥራ ሂደት በቀጥታ ወደ መጨረሻው ጥፋት የሚራመራን ነው። ይህንን እውነታ ለመቅረፍና ለመወጣት፤ ሀረሪዎች የእርዳታ ጥሪ እያቀረቡ ሲሆን፤ ለተሻለ ኑሮና ብሩህ ጊዜ በአንድነት መስራት የሁሉም ሀረሪዎች ግዴታ መሆኑን እናሳስባለን።

10. በታሪክ ዘመናት ሁሉ፤ ወጣቶች የሕብረተሰቡን ችግር ተሸክመው በማህበረሰባቸው ውስጥ ያለውን አሳዛኝ እውነታ ለመለወጥ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል። የሀረሪ ወጣቶች፤ ሁላችንም የምናልመውን ማህበረሰብ እውን ለማድረግ፤ የሀላፊነት ችቦውን ለማቀጣጠል መዘጋጀታቸውን፤ የሀረሪ ትብብር ተገንዝቧል። በክልሉ የሥራ አጥነት መጠን እያሻቀበ ባለበት ሁኔታ፣ የኤኮኖሚ ልማት ይኖራል ብሎ ማሰብ የቻል አይደለም። አሁን በሐረር ክልል ያለው እውነታ፤ የሐረሪ ኮሌጅ ምሩቃን እንኳን ትርጉም ያለው ሥራ ለማግኘት የተቸገሩበት ጊዜ ነው። ስለሆነም፤ የሐረሪ ተወላጆችም ሆኑ የክልሉ ባለስልጣናት፤ የሐረር ኢኮኖሚ ልማት አካል በመሆን ወጣቱን ወደ ስራ ዓለም እንዲይስገቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በሀገር ወስጥና በውጭ ሀገር ያለን ሀረሪዎች፤ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን ብሎም ለእናት ሀገራችን ስንል፤ ይህን ጥሪ ለመመለስ ዝግጁ መሆን አለብን።

የሀረሪ ትብብር ለፍትህና እኩልነት (HAJE)